Quantcast
Channel: Welcome to bilisummaa
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1337

የአቶ ዳዉድ አነጋገር በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ምን ማለት ነዉ?

$
0
0
Taye Dendea

ብዙ ፓርቲዎች ከዉጭ መግባታቸዉ ይታወቃል። አመጣጣቸዉ ደግሞ ለኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ከመስጠት አልፎ ከመንግስት ጋር መስማማትን ያካትታል። ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር ላይ የተመሠረተ ነዉ። ሁሉም በሰላም እና በህግ መሠረት አላማዉን ለማሳካት መምጣቱ እሙን ነዉ ። ይህ ጉዳይ ትጥቅ መፍታትን ይጨምራል። ምክንያቱም አንድ ፓርቲ ጠመንጃ ይዞ ለሰላማዊ ምርጫ መወዳደር አይችልም። ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በእኩል ሜዳ ላይ መንቀሳቀስ አለባቸዉ። አንዱ ታጥቆ ሌላዉ ባዶ እጁን ከሆነ ደግሞ እኩልነት የለም። ስለዝህ ከመንግስት ዉጭ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትጥቅ መፍታታቸዉ አግባብ ነዉ።

በዝህ ጉዳይ ላይ አቶ ዳዉድ ኢብሳ የሰጡት ሀሳብ ህግን እና ሎጅክን የሚቃረን ነዉ። ዋልታ TV እንዳስነበበን አቶ ዳዉድ “ትጥቅ የሚፈታም የሚያስፈታም የለም” ብሏል። የዝህ ትርጉም ሰፊ ነዉ። ግን ሁለት ነገሮች በሚገባ መታየት አለባቸዉ። አንደኛዉ መንግስትን ዕዉቅና መንፈግ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት የሚባል ነገር የለም እንደማለት ይመስላል። ትጥቅ የሚያስፈታ የለም ማለት መንግስት የለም ከማለት አይተናነስም። ሁለተኛዉ ደግሞ ህገ-ወጥነት ነዉ። ንግግሩ አቅም ስላለን ህግንም ሆነ መንግስትን አናከብርም እንደማለት ይመስላል። ትጥቅ የሚፈታ የለም ማለት ህገ-መንግስቱንም ሆነ ሌሎች ህጎችን አናከብርም ማለት ይሆናል። በጣም ገራሚ ጉዳይ ነዉ። መንግስትን ዕዉቅና መንፈግ እና ህግን አለማክበር ምን ይባላል? ለኢትዮጵያ መንግስት እዉቅና ካልሰጡ እና ህግን የማያከብሩ ከሆነ ከአስመራ ለምን መጡ?
ለማንኛዉም የኢትዮጵያ መንግስት መኖሩን ማወቁ አይከፋም። ህገ-መንግስቱን እና ሌሎች የሀገሪቱን ህጎች ማክበርም ግድ ይላል። መንግስትን እና ህግን መቀየር ይቻላል! ህገ-መንግስቱም ይፈቅዳል። ነገር ግን ህጋዊ አካሄድን መከተል ያስፈልጋል። ከህግ ዉጭ መሄድ ለማንም የማይጠቅም አማራጭ ይሆናል።

የህግ የበላይነት ይከበራል!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1337

Trending Articles


Girasoles para colorear


mayabang Quotes, Torpe Quotes, tanga Quotes


Tagalog Quotes About Crush – Tagalog Love Quotes


OFW quotes : Pinoy Tagalog Quotes


Long Distance Relationship Tagalog Love Quotes


Tagalog Quotes To Move on and More Love Love Love Quotes


5 Tagalog Relationship Rules


Best Crush Tagalog Quotes And Sayings 2017


Re:Mutton Pies (lleechef)


FORECLOSURE OF REAL ESTATE MORTGAGE


Sapos para colorear


tagalog love Quotes – Tiwala Quotes


Break up Quotes Tagalog Love Quote – Broken Hearted Quotes Tagalog


Patama Quotes : Tagalog Inspirational Quotes


Pamatay na Banat and Mga Patama Love Quotes


Tagalog Long Distance Relationship Love Quotes


BARKADA TAGALOG QUOTES


“BAHAY KUBO HUGOT”


Vimeo 10.7.0 by Vimeo.com, Inc.


Vimeo 10.7.1 by Vimeo.com, Inc.



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>